Ethiopian Ortodox Tewahedo

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ይህ የፌስቡክ ገጽ በእግዚያብሄር እርዳታና በድንግል ማርያም አማላጅነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንና ክርስቲያኖችን አንድነት ለመጠበቅ ይሰራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የቤተክርስቲያኒቱ ዶግማና ቀኖና እንዲጠበቅም የራሱን አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም በዚህ ገጽ ላይ የሚወጡ ጽሁፎች፤ ፎቶዎች፤ ቪዲዮዎች እና ማንኛውም ዶክመንት የቤተክርስቲያኒቱን አንድነት፤ ዶግማ፤ ቀኖናና ትውፊት የሚጠብቅ መሆን ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በመለስ በተለያዩ የቤተክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ሃሳቦች በጨዋነት መንፈስ ሊንሸራሸሩ ይችላሉ፡፡ ይህ ገጽ ክርስቲያናዊ በመሆኑ የሚወጡት አስተያየቶችም ሆኑ ጽሁፎች በክርስቲያናዊ ስነምግባር ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ ይጠበቃል፡፡ በመሆኑም የሚወጡት ጽሁፎችና አስተያየቶች ማንንም ሰው የማይሳደቡ፤ የማይዘልፉ፤ የማያንቋሸሹ መሆኑ ብቻ ሳይሆን በአክብሮትና መግባባት እንዲሁም ሌላውን የሚያንጹ መሆን ይገባቸዋል፡፡
በመሆኑም የእኛ በሆነው ገጽ ኦርቶዶክሳዊ በሆነ ጠባይ እንሳተፍ፤ እንማማር፤ እንወያይ፤ የቤተክርስቲያናችንን አንድነት፤ ዶግማ፤ ቀኖናና ትውፊት እንጠብቅ! አንድነታችንን እናጠናክር!
+የመጀመሪያ እምነታችንን እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ፥ የክርስቶስ ተካፋዮች ሆነናልና፤ ወደ ዕብራውያን + 3፥14
+እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለምሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም። + ዮሐ 5፥24

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ this page
ራእይ

አመጽን የናቀ፣ ክፋትን የጠላ፣ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞች የራቀና እንደቃሉ የሚኖር ፍጹም ለበጎ ሥራ የተዘጋጀ በጎ ትውልድ በተዋሕዶ ጥላ ሥር ማየት፡፡

አላማ

* የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት የሆነበትን ፍጥረታዊ ሰው ከሰው ባልሆነ ምክር እውነትን ወደማወቅ ማምጣትና እግዚአብሔርን በማመን የመንፈሳዊ ሰው ኑሮን እንዲኖር ማስቻል፡፡

* ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ከሚሰጡ ቅዱሳት መጻሕፍት የጥበብን ቃል ለትውልዱ ማካፈል፡፡

* ትውልድን በቃሉ ወተት አሳድጎ ፍጹም ለበጎ ሥራ ማዘጋጀት፡፡

* መከራ በበዛበት ዓለም የሚኖሩ አማኞችን በቃሉ በማጽናት ወደ ፍጻሜ ማድረስ፡፡

ተልዕኮ

* የአባቶችን እውነተኛ አስተምህሮ በትውልዱ ቋንቋ ለትውልዱ መግለጥ!!!