GOSPEL 4 ETHIOPIA

‹‹እንዲህም አላቸው፡- ‹ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ›፡፡››
የማርቆስ ወንጌል 16፡15

ውድ የ ‹‹የምሥራቹ ቃል›› ማኅበር አባላት፣ በተለይም የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስን የምታውቁ፣ ዳግም ከውሃና ከመንፈስ የተወለዳችሁና ዓለማት ሳይፈጠሩ፣ ተራሮችና ኮረብቶች ሳይፀነሱ በጌታ ኢየሱስ በኩል በእግዚአብሔር የተመረጣችሁ ቅዱሳን፣ በጌታችንና በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም የከበረ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ፤
እንደምታውቁት የማኅበራችን ዋነኛ ዓላማ ታላቁን ተልዕኮ ከዳር ለማድረስ ነው፤ ያም በማርቆስ ወንጌል 16፡15-16 ላይ የተጻፈውንና ጌታችንንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያዘዘውን ‹‹ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፣ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ፡፡›› የሚለውን ነው፡፡
አዎ፣ መከሩ ነጥቷል ሠራተኞች ግን አንሰዋል እንደሚል… ፍጥረት ሁሉ የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ የሚጠብቅበት ሰዓት ይህ ነው፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጆች ምን ያህል ታላቁን ተልዕኮ ባገኙት መንገድ ሁሉ እያደረሱ ነው ብለን ስንጠይቅ መልሱ አንድና አንድ ነው፤ … አመርቂ አይደለም፡፡
እግዚአብሔር በአንድም በሌላም መንገድ ሰዎች እንዲድኑ ይወዳል፣ እንደየዘመኑም ልዩ ልዩ የደህንነት መንገዶችን ያዘጋጃል፤ በተለይም በዚህ ዘመን ‹‹የቴክኖሎጂ ዘመን›› እንደመሆኑ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች እንደ ቴሌቪዥን፣ ሬድዮ፣ ኢንተርኔትና የመሳሰሉት ለወንጌሉ ሥርጭት ትልቅ ሚና ይጫወታሉ፡፡
ረጅም ዕድሜና ጤና እንዲሁም የዘላለም ሕይወት ለኢንተርኔትና በተለይም ለፌስቡክ ጠበብቱ ይግባቸውና፣ ዕነሆ በፌስቡክ ትውልዳችንን በወንጌል ልንደርስ አሀዱ ብለናል፡፡
ስለዚህም አንዳንድ የ ‹‹ የምሥራቹ ቃል›› ማኅበር አባላት እንደሚያደርጉት ጌታን የማያውቁና ዳግም ያልተወለዱ ወዳጆቻንና ዘመዶቻችንን ወደ ማኅበሩ መቀላቀልና ከምስራቹ የህይወት ቃል ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ማድረግ ከሁላችንም የሚጠበቅ ከመሆኑም ባሻገር ለታላቁ ተልዕኮ ጥሪ ምላሽ መስጠት ነው፡፡
ስለዚህም ባጭር አነጋገር የሚከተሉት አስር ነጥቦች ከእኛ ስለ ሚጠበቀው ና ስለ ማይጠበቀው ነገር ያስረዳሉ፣

እንድናደርግ የሚጠበቀው

1. ያልዳኑ ወዳጅ ዘመዶቻችንን ወደ ማኅበሩ መቀላቀል (‹‹አድ›› ማድረግ)፣
2. ላልዳኑ ሰዎች ብቻ የሚሆን የመጽሀፍ ቅዱስ ቃል (ጥቅስ)፣ ልዩ ልዩ ምስክርነቶች ያዘሉ ጽሁፎችና ምስሎች ወይም ቪዲዮና ኦዲዮ በማኅበሩ ‹‹ዎል›› ላይ መለጠፍ (‹‹ፖስት›› ማድረግ)፣ ወይም ዶክመንት ማድረግ፣
3. ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ጥያቄዎች፣ አስተያየቶችና የመሳሰሉት ቢኖሩ ‹‹ፖስት›› ማድረግ፣
4. በማኅበሩ ውስጥ ያለን የእግዚአብሔር ሰዎች መንፈስ ቅዱስ በረዳን መጠን የምናውቀውንና የተረዳነውን ብቻ ለሚጠየቁት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከመጽሐፍ ቅዱስ በማጣቀስ ትክክለኛውን ምላሽ መስጠት፣
5. ሰዎች እኛ ያገኘነውን ታላቅ መዳን ያገኙ ዘንድ መፀለይ ና
6. ቢቻል ደግሞ የስልክ ቁጥር በመለዋወጥ በአካል የምስራቹን ቃል ማካፈል ነው፡፡

እንዳናደርግ የማይጠበቀው

1. የ ማኅበራችን ዋነኛ ዓላማ ወንጌልን ለአዳዲስ ነፍሳት ማድረስ እንደመሆኑ ለአዳዲስ ሰዎች የማይገቡና በቀላሉ ሊረዷቸው የማይችሏቸውን ነገሮች አለመለጠፍ፣
2. አላስፈላጊና ከምስራቹ ቃል (ከወንጌሉ) ጋር ተያያዥነት የሌላቸውን አጀንዳዎች አለማንሳት
3. ከወንጌሉ ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነት የሌላቸውን ምስሎች፣ ጽሁፎች፣ ኦዲዮና ቪዲዮ ፋይሎች የመሳሰሉትን አለመለጠፍ፣
4. የሌሎችን ኃይማኖትና መንገድ የሚነኩና ክብረ-ነክ የሆኑ ገለፃዎችንና አስተያየቶችን ከመስጠት መቆጠብ

እግዚአብሔር ይባርካችሁ!...
በክርስቶስ ወንድማችሁ ዳዊት ወርቁ
የማኅበሩ አስተዳዳሪ


"And he said unto them, Go ye into all the world, and preach the gospel to the whole creation."

(Mark 16:15)

Dear and respected 'The Gospel’ members, I would like to greet you in the name of Jesus Christ, our Lord and Savior, Amen.
I am writing this message for all members, particularly for those of you who are borne again Christians, and chosen to be the Son of God through Jesus Christ before the world was created.
As you all know, the main purpose of the “The Gospel” group is to accomplish the great mission, which is written on the gospel of Mark 16:15, ordered by our Lord and Savior Jesus Christ, the Son of God.
God needs sinners to be saved either in one way or another.
Long life to the inventors of internet, mainly for the FACEBOOK developers, the technology has played a big role regarding preaching the gospel to the whole nations. That is why I have decided to reach my generation through FACEBOOK.
Don’t be amazed if I request and add the person I never know to the group violating the rules and regulations of the FACEBOOK.
I got a wonderful salivation through Jesus Christ and it’s my responsibility to share this great salivation to all Ethiopians, men and women, literate and illiterate, religious and atheist.
For that reason, as a few of the group members do, it is our duty also to add our unsaved friends to the “The Gospel ” group.
If you do this, really you are giving the right response to the call of the great mission.
Consequently, the following ten “DO” and “DO NOT DO” points are expected from all of us:

DO
1. Add unsaved friends to the group.
2. Post Biblical quotations to the unsaved ones.
3. Post different spiritual questions, opinions and the like to the unsaved people.
4. Give Biblical answers and resolutions to any questions, posted on the group wall.
5. Pray to unsaved people to have the great salivation through Jesus Christ, the Son of God and
6. If possible, ask telephone number and share the good news in person.

DO NOT DO
1. Do not post any difficult quotations to unsaved people.
2. Do not use the group wall for unnecessary issue which is not related to the gospel.
3. Do not post any pictures, video, audio and the like files that do not able to express the gospel.
4. Don’t use offensive and pessimistic explanations that degrading and disrespectful others religion.

God bless you
Dawit Worku
Admin of the Group